ክፍል 2 ይቅር አለማለት
እንኳን ለመሮጥ ለመራመድ እንኳን እግሬ አስቸገረኝ። ከውጪ ሲታይ ምንም ችግር ያለበት አይመስልም ግን ይቆረቁረኛል፣ ከመሮጥም ከልክሎኛል። ዓላማና ግብ አለኝ መድረስ ያለብኝ፥ ታዲያ እንዴት አድርጌ ነው ወደዛ የምደርሰው? ከማሰብና ከመመኘት ውጪ።
እጅግ ሲከፋ ጫማዬን ሳወልቅ አስደንጋጭ ነገር ነበር ያየሁት። በጣም ትንንሽ ከሆኑ ጀምሮ ጥቂት ያይደሉ ጠጠሮች ጫማዬ ውስጥ ነበሩና! እነርሱ ነበሩ እየቆረቆሩ አላራምድ ያሉኝ። ትንሽ የተባለችዋ ጠጠር እንኳን በጣትና በጣቴ መካከል ገብታ እንቅፋት ሆናብኛለች። ተለቅ ያለውንማ ያመንኩት የካደኝን የታመንሁ የጎዳኝ የእንቶኔን ነገር ያንገበግበኛል ይለበልበኛል።
አዎን ይቅር አለማለትም ጫማ ውስጥ እንዳሉ ጠጠሮች ነው። አይመች ፣ እንደልብ አያራምድ። ከዓላማ የሚያዘግይ ወደ ግብ ለመገስገስ እንቅፋት ከመሆን በቀር ምን ፋይዳ አለውና? ሰዎች የበደሉን በደል ሳያንስ ይቅር ባለማለታችን መንፈሳዊ በረከታችን ተይዞ ይበልጥ ተጎድተንበታል።
ወደ ታሪኬ ልመልሳችሁና ጥርግ አድርጌ ጠጠሮቹን ከጣልሁ በኋላ ጥሩ ምቾት ተሰምቶኝ ከመራመድ አልፌ እንደቀድሞው ወደ ግቤ መገስገሴን ቀጠልሁ።
አዎን ስለምን እየተቸገርን ከተጠራንበት መጠራት፣ ልንደርስ ካለን ግብ እንዘገያለን? የተቀበልነውን ምህረት የተደረገልንን ይቅርታ ልክ አስበን እኛም የበደሉንን ይቅር ብለን መልካሙን የእምነትን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ።
አዎን ይቅር አለማለት ጫማ ውስጥ እንዳለ ጠጠር ነውና በይቅርታ እንመላለስ።
ይቀጥላል
This Post Has One Comment
so true brother! even if it not easy to forgive someone who hurts a lot but as christians we should let go unforgiveness. Our lord also order us in the bible Mark 11:25 ” .. whenever you stand praying, forgive, if you have anything against anyone, so that your Father also who is in heaven may forgive you your trespasses.”
Comments are closed.